Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ሕዝብ ጁንታውን በመቃወም በነገው ዕለት ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ሕዝብ የሕወሓት ጁንታን በመቃወም በነገው ዕለት (ሐምሌ 15 ቀን 2013 ዓ.ም) በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

ሰላማዊ ሰልፉ ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ እስከ አጋማሽ ቀን የሚካሄድ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ የኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አብዲ ፀጋዬ ገልጸዋል።

ሰልፉ የሕዝቡን ጥያቄ መሠረት በማደረግ የሚካሄድ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ የሰልፉ ዓላማ ጁንታውን ከመቃወም ባለፈ ሕዝቡ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያለውን ደጀንነት ለመግለጽ ነው ብለዋል።

6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁ እና የሕዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት በስኬት መከናወኑን ጨምሮ እስካሁን በሀገር ደረጃ የተገኙ ድሎች የሚወደሱበት መሆኑንም የጽ/ቤቱ ኃላፊ አብዲ ፀጋዬ መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.