በጎንደር ከተማ 96 በመቶ ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች ናቸው
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ 96 በመቶ ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች በመሆናቸው የማሻሻያ ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡
ከተማ አሰተዳደሩ ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ህዝቡንና የልማት ድርጅቶችን በማስተባበር ደረጃ የማሻሻልና አዲስ ትምህርት ቤቶችን እየገነባ ነው።
በጎንደር ከተማ የሚገኘው የአየር ጤና አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለ አስራ አምስት የመማሪያ ክፍል ግንባታ በ16 ሚሊዮን ብር እየተገነባ ይገኛል፡፡
የትምህርት ቤት ግንባታውን አማራ ልማት ማህበር ከዳሽን ቢራ ፋባሪካ ጋር በመተባበር እንደሚያሰገነባው የፋብሪካው የማህበረሰብ ዘርፍ መምሪያ ስራ አስኪያጅ አቶ እንዳልካቸው አበበ ተናግረዋል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ድርጅቱ በአማራ ክልል በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሚታየውን ችግር በመረዳት በደብረብርሃን ከተማ፣ በደቡብ ጎንደር ደራ እና ጎንደር ከተማ 50 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ስራ እያከናወነ ነው።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ በ2013 በጀት ዓመት 19 ከደረጃ በታች ትምህርት በቶች ተለይተው የአስሩ ትምህርት ቤትች ግንባታ እየተካሄደ ነው ብለዋል።
የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት የትምህርት ቤቱ መገንባት በተማሪዎች የትምህርት አቀባበል ላይ በጎ ተፅዕኖ ይኖረዋል ብለዋል።
የአማራ ልማት ማህበርም የከተማውን ትምህርት ቤቶችን የጥራት ደረጃ ለማሻሻል ጥረት እያደረገ ነው ተብሏል።
ምናለ አየነው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!