Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ እና በተመድ መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት በየዘርፉ መጠናከር አለበት-ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፖለቲካ እና የሠላም ግንባታ ጉዳዮች ምክትል ሀላፊ ሮዝመሪ ዲካርሎ ጋር ተወያዩ ።
ውይይቱም በትግራይ ስላለው ሁኔታ ፣ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ፣ በኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይ ፣ በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ እና በኢትዮጵያ እና የተመድ ግንኙነት ላይ ያተኮረ ነበር።
6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በቅርብ መከታተላቸውን ያነሱት ዲካርሎ፥ በሠላም በመጠናቀቁም እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።
ፕሬዘዳንት ሣህለ ወርቅ በጉዳዮቹ ላይ ማብራርያ የሰጡ ሲሆን፥ በኢትዮጵያ እና በተመድ መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት በየዘርፉ ማጠናከር እንደሚገባ አስምረውበታል።
ድርጅቱ ግጭቶች ከመከሰታቸው በፊት መግታት ላይ ብዙ ሊሠራበት እንደሚገባ ያላቸውን እምነት መግለጻቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.