45 ዶክተሮች እና የህክምና ባለሙያዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ሙያዊ ድጋፍ ለመሰጠት ወደ ግንባር አቀኑ
አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ ሆስፒታሎች የተውጣጡ የህክምና ባለሙያዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ በዛሬው ዕለት በመስቀል አደባባይ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡
የጤና ቢሮ ኃላፊው ዶክተር ዮሀንስ ጫላን ጨምሮ 45 ዶክተሮች እና የህክምና ባለሙያዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ ዛሬ ሽኝት ተደርጎላቸዋል።
ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቀነአ ያደታ ፣የሀገር ሽማግሌዎች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ለባለሙያዎቹ አሸኛኘት ተደርጓላቸዋል ።
የህክምና ባለሙያዎቹ ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት መድሀኒቶች እና የህክምና ቁሳቁሶችን ይዘው ተጉዘዋል።
ከዚህ ቀደም በሁለት ዙሮች ከከተማዋ የተለያዩ ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች የተውጣጡ ዶክተሮች እና የህክምና ባለሙያዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ ወደ ትግራይ ክልል መጓዛቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!