የጉጂ ዞን በአካባቢ ጥበቃ ጠንካራ ባህል ያለው ነው – አቶ አድማሱ ዳምጠው
አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 22፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ጨምሮ የዋልታ ቲቪ እና ዋፋ ማርኬቲንግና ኘሮሞሽን ሁለተኛው ቀን የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በጉጂ ዞን በአዶላ ከተማ ተከናውኗል።
ዛሬ በአዶላ ከተማ የሚገኙ የአቅመ ደካማ ሰዎችን መኖሪያ ቤት መልሶ የመገንባት መርሃ ግብር ተካሂዷል።
በመቀጠልም የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ይካሄዳል።
በዚሁ ወቅት ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ አድማሱ ዳምጠው ፥ የአካባቢው ህብረተሰብ በጉጂ ገዳ ስርዓት በመደጋገፍ ፣ በመተሳሰብና በመረዳዳት የሚኖር ነው ብለዋል።
አካባቢው ባህሉን ፣ታሪኩን እና እሴቱን ጠብቆ እና ተንከባክቦ ያቆየና ከአካባቢው አልፎ ለሀገርም ኩራት የሚሆን መሆኑንም ተናግረዋል።
እኛም ይህንን የመረዳዳት ባህል ለማገዝ ወደዚህ መጥተናል፣ አኩሪ ባህል በአካል በማየታችን ደስተኞች ነን ነው ያሉት።
የአዶላ ምክትል ከንቲባ አቶ ኡቱራ ኢመዮ መገናኛ ብዙኀን በአካባቢው ተገኝተው የበጎፈቃድ ስራዎችን መከወናቸው በማህበረሰቡ መነቃቃትን ይፈጥራል ብለዋል።
በዚህ ዓመት በከተማው 24 የአቅመ ደካሞችን ቤት ለማደስ ታቅዶ 10 ያህሉ መገንባት መጀመራቸውን ገልፀዋል።
ችግኞችን ከመትከል ባለፈ እንዲፀድቁ በተሰራው ሥራም ባለፉት አመታት የተተከሉ ችግኞች ወደዛፍነት መቀያራቸውን አመላክተዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉ የመገናኛ ብዙሃን ሀላፊዎች በበኩላቸው ፥ ህብረተሰቡን በልማቱ ስራ ማገዛቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
በመሰረት ደምሱ እና አፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!