በምክር ቤቱ የሪፎርም ስራዎች ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ምሁራን እውቅና ተሰጠ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሪፎርም ስራዎች ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ምሁራን እውቅና እና ሽልማት ተሰጣቸው፡፡
በዛሬው እለት እውቅና የተሰጣቸው የህግ ማርቀቅ ስርዓት ጥራትን የሚያስጠብቅ መመሪያ ዝግጅት ተሳተፉ የህግ ምሁራን ናቸው፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የእውቅና የምስክር ወረቀትና ሽልማቱን ባበረከቱበት ወቅት÷ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ከምሁራን ጋር ተቀራርቦ መስራት በመቻሉ ምክር ቤቱን ለማዘመን የሚያስችሉ በርካታ ግብኣቶችን ማግኘት መቻሉን ገልጸዋል፡፡
እውቅና እና ሽልማት የተሰጣቸው ዶክተር ኤሊያስ ኑር፣ አቶ ሽፈራው ወልደሚካኤል፣ አቶ ዘነበ ቡልቃ እና አቶ ዘካሪያ ኤርኮላ መሆናቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!