Fana: At a Speed of Life!

ለኢትዮጵያ መሞት ውርደት ሳይሆን ጌጣችን ነው – ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገርና ህዝብን የመከላከል ጦርነት ለኛ አዲስ አይደለም፤ ለኢትዮጵያ መሞት ውርደት ሳይሆን ጌጣችን ነው ሲሉ የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረ ኃይል ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ገለጹ፡፡

በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ አሸባሪው የህወሀት ጁንታ በስልጣን ዘመኑ አጋርና አናሳ ብሄር በሚል የዜጎችን መብት ሲገድብ የኖረ ሀይል እንደነበረ የግልገል በለስ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

ይህን አሸባሪ ሀይል ለአንድ ጊዜ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ ከሀገር መከላከያና ከመንግስት ጎን ተሰልፈው እንደሚፋለሙት ቃል ገብተዋል፡፡

ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ በበኩላቸው፥ ህውሀት እየፈፀመ ያለው ሀገር የማፍረስ ተግባር ከምስረታው ጀምሮ በአላማ የያዘውና ወቅት እየጠበቀለት የነበረ የረጅም ጊዜ እቅዱ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ ዘመቻ ላይ የመንግስትን ጥሪ ተቀብለውና ስልጠና በመውሰድ ወደ ህዝቡ የተቀላቀሉ ታጣቂዎች ዋነኛ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ማቅረባቸውን ከመከላኬ ሰራዊት ሚኒሰቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.