ዶ / ር እዮብ ተካልኝ ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ከሳፋሪኮም የኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አንዋር ሶሳ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ ሳፋሪኮም አሁን ያለበትን ደረጃ እና ወደፊት በሚያከናወናቸው ስራዎች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለግሉ ዘርፍና ለውጭ ኢንቨስትመንት ገበያዋን መክፈቷን ጠቅሰው፥ የውጭ ኢንቨስትመንት ለተጠቃሚዎች የላቀ የአገልግሎት፣ ጥራት እና ሰፊ አማራጭን ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።
በመንግስት የተወሰደው ማሻሻያዎች ወደፊት በዘርፉ ለሚደረገው ሽግግር መሰረት የሚጥል መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
የሳፋሪኮም የኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አንዋር ሶሳ በበኩላቸው፥ መንግስት ሳፋሪኮም በዘርፉ እንዲሰማራ ለሰጠው ይሁንታና ለተደረገለት ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው መግለፁ የሚታወስ ሲሆን ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት የቀረበውን ጨረታ በማሸነፉ የኢትዮጵያ የኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ፈቃድ እንዲሰጠው የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።
ይህን ተከትሎ ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ ሳፋሪኮም ከኬንያ ፣ቮዳፎን ከብሪታኒያ ፣ቮዳኮም ከከደቡብ አፍሪካ፣ ሲዲሲ ግሩፕ ከብሪታኒያ፣ ሰሚቶሞ ኮርፖሬሽን ከጃፓን በጥምረት የያዘ የቴሌኮም ድርጅት ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!