Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ጸሃፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ጸሃፊና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም በትግራይ ክልል ስላለው የጸጥታና የሰብዓዊ እርዳታ ሁኔታ ዙሪያ መምከራቸው ነው የተገለጸው፡፡
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ አሳሳቢ የሆኑትን ሰብዓዊ ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ከተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡
ግሪፊትስ በበኩላቸው የመንግስታቱ ድርጅት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ፍላጎቶች በሚያሟላ መልኩ መስራት እንደሚፈልግና ከሀገሪቷ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰራ መናገራቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.