ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሊምፒክ በ10 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር በሰለሞን ባረጋ አማካኝነት የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘቷ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ለቀሩት ተወዳዳሪዎችም መልካም ዕድል እመኛለሁ ብለዋል።
ኢትዮጵያ የገጠሟትን ፈተናዎች በማለፍ ድል ማስመዝገቧን ትቀጥላለችም ነው ያሉት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!