ህይወቱን ለሚሰዋልን መከላከያ ሰራዊት የምንሰስተው ነገር የለም- የጅማ ከተማ ደም ለጋሾች
አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ህይወቱን ለሚሰዋልን መከላከያ ሰራዊት የምንሰስተው ነገር የለም ሲሉ የጅማ ከተማ ደም ለጋሾች ገለጹ፡፡
“ህይወቱን ለሚሰዋልኝ ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ደሜን አሰጣለሁ” በሚል መሪ ቃል በጅማ ከተማ የደም ልገሳ መርሀ ግብር እየተካሄደ ነው።
ደም እየለገሱ ያሉ ወጣቶች፥ የሀገርን ህልውና ለማስከበር ለቆመው የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ የምንሰስተው ነገር የለም ብለዋል።
ወጣት ኢዘዲን ከማል፥ ለመከላከያ ሰራዊት ደም አይደለም ህይወቴን አሳልፌ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ ሲልም ነው የገለጸው።
“ኢትዮጵያን በአንድነት ሀገርን ከጥቃት ተከላክለን ሰላማዊና የለማች ሀገር ለመገንባት መስራት ይጠበቅብናል” ሲል አመልክቷል።
“መከላከያው በሁሉም ረገድ መደገፍ አለበት” ያለው ወጣት ኢዘዲን ደም መለገስም ሆነ ሌሎች ድጋፎችን ማድረግ ወቅቱ የሚጠይቀው ተግባር መሆኑን መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።
መከላከያን ለመደገፍ የምንሰስተው ነገር አይኖርም ያለው ሌላው ወጣት አብዱልባሲጥ ሼነዚፍ ሲሆን፥ ደም በመለገስ መከላከያን መደገፍ ግዴታ ጭምር መሆኑን ተናግሯል።
ሁሉም ሰው ለመከላከያ ሰራዊት በፍቃዱ የበኩሉን ማድረግ እንደሚኖርበት የገለጸው ወጣቱ፥ ወጣቶች ደማቸውን በመስጠት አጋርነታቸውን ማሳየት እንዳለባቸው አስገንዝቧል።
የጅማ ደም ባንክ አስተባባሪ አቶ ሀይደር ኡመር ህብረተሰቡ ለመከላከያ ደሙን በመለገስ አጋርነቱን እየገለጸ ያሉ ሲሆን፥ ከትላንት በስትያ የተጀመረው የደም ልገሳ መርሀ ግብር ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቀዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!