እርዳታ ተከለከልኩ የሚለው አሸባሪ ድርጅት የእርዳታ እህል የተከማቸባቸውን መጋዘኖች አቃጥሏል
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) እርዳታ ተከለከልኩ የሚለው አሸባሪ ድርጅት የእርዳታ እህል የተከማቸባቸውን መጋዘኖች ማቃጠሉ ተገለፀ፡፡
የመንግስትን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ወደ ጎን በመተው በአፋር እና በአማራ ክልሎች ላይ ትንኮሳ እየፈጸመ ያለው አሸባሪው ሀወሓት በአንድ በኩል እርዳታ እንዳይደርስ ተከለከልኩ በማለት ይጮሃል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የእርዳታ እህል የተከማቸባቸውን መጋዘኖች ማቃጠሉ ተገልጿል፡፡
ከስር የተያያዘው ምስል ላይ የሚታየው ሀቅም የሚያረጋግጠው ይሄንኑ ነው።
አሸባሪው ሰሞኑን በአፋር ክልል የነበረንና የእርዳታ እህል የተከማቸበትን መጋዘን አቃጥሏል።
የዚህ አሸባሪ ቡድን ዓላማ ግልጽ ነው፤ በትግራይ ህዝብ ስም የራሱን የኖረ ጥቅም ማስከበር።
መንግስት የማሰቢያ ጊዜ የሰጠው የትግራይ ህዝብ በአሁኑ ወቅት በአሸባሪው ድርጅት አመራሮችና ካድሬዎች ተማሯል፤ በየከተሞች ህዝቡ ጥያቄ እያነሳ ይገኛል፤ልጆቻችንስ ማለትም ጀምሯል።
የአሸባሪው አመራሮች ደግሞ ልጁን ያልሰጠ እርዳታ አያገኝም በሚል ከህዝቡ ጋር ፍጥጫ ውስጥ መግባታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
ይህ ቡድን ህጻናትን ሳይቀር ወደ ጦርነቱ እየማገደ ሲሆን፤ በቅርቡም በአፋር ክልል ሶስት ብርጌድ ታጣቂዎቹ መደምሰሳቸው ይታወሳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!