Fana: At a Speed of Life!

“የባንዳዎችን አገር የማፈራረስ ምኞት ለመመከት ሕዝቡ በአንድነት መቆም አለበት”-አቶ ታገሰ ጫፎ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለመከላከያ ሠራዊቱ ደም ለገሱ፡፡

በዚህ ወቅት የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የባንዳዎችን አገር የማፈራረስ ምኞትና የውጭ ኃይሎች በጣልቃ ገብነት የሚያደርጉት ወረራዎችን ሕዝቡ በአንድነት ቆሞ ምኞቻውን ሊያከሽፍ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
አያይዘውም ኢትዮጵያ የሌሎችን አገሮች ጥቅም ያለአግባብ መውሰድ እንደማትፈልግ ሁሉ የራሷንም ጥቅም አሳልፋ እንደማትሰጥ አውቀው የውጭ ወራሪ ኃይሎች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
“የምንሄድበት መንገድ ጤናማ ግን ውስብስብ በሆነ ሁኔታ የምናልፍበት ነው” ያሉት አፈ ጉባዔው፤ የኢትዮጵያን የመልማት እንቅስቃሴየማስተጓጎል ጥረት እየተደረገባት እንደሆነ አንስተዋል።
ይሁንና ኢትዮጵያዊያን በአንድነትና በፅናት ቆመው ይህን ችግር ለመሻገር እያደረጉት ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።
አፈ ጉባኤ አታገሰ ጫፎ የምክር ቤቱ ሴት አባላት ለሠራዊቱ ስንቅ እያዘጋጁ መሆኑን፤ ከሠራተኞች መካከልም ወደ ግንባር ለመዝመትጥያቄ ያቀረቡ መኖራቸውንም ጠቁመዋል።
ወራሪውን ኃይል ለመመከት በትናንትናው ዕለት የምክር ቤት አባላትና የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት ሠራተኞች የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለመከላከያ ሠራዊቱ ድጋፍ መለገሳቸውን ያስታወሱት አቶ ታገሰ ÷ በዛሬው ዕለት ደግሞ ደማቸውን እየለገሱ መሆኑን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.