Fana: At a Speed of Life!

የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ለመስጠት ቃል ገቡ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ አመራር ሰራተኞች እና መምህራን ለሀገራዊ ጥሪው ምላሽ በመስጠት ለመከላከያ ሰራዊት ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ለመስጠት ቃል ገቡ።
የዩኒቨርስቲው መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች የአንድ ወር ደሞዛቸውን ወይም ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ከመስጠት ባለፈ የደም ልገሳ መርሃ አከናውነዋል።
የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ንጉስ ታደሰ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ሀገር የገባችበትን ችግር ለመወጣት በጋራ መቆም ይጠበቅብናል ሲሉ የግቢው ማህበረሰብ ለድጋፉ ያሳየውን ትብብር እና የባለቤትነት ስሜት መቀጠል ይገባዋል ብለዋል።
ያነጋገርናቸው መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች እንዳሉት ሁሉም የሚኖረው ሀገር ሰላም ሲሆን ነውና ለሀገር ህልውና የሚጠበቅብንን እንወጣለን፤በሙያችን፤ በእውቀት እና በገንዘባችን በቀጣይም ድጋፉን እንቀጥላለን ብለዋል።
በኤልያስ ሹምዬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.