Fana: At a Speed of Life!

3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ከኮንትሮባንድና ህገ ወጥ ንግድ ማጭበርበር ማዳን ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው በጀት አመት 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ከኮንትሮባንድና ህገ ወጥ ንግድ ማጭበርበር ማዳን መቻሉን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የኮንትሮባድ እንቅስቃሴንና ህገ ወጥን ንግድ ማጭበርበርን በቅንጅታዊ አሰራር ለመከላከል በ2013 በጀት አመት የተሰሩ ስራዎችን አስመልክቶ የጉምሩክ ኮሚሽን ከፌደራል ፖሊስ አመራሮች ጋር ምክክር አድርጓል፡፡
በውይይቱም ኮሚሽኑ በበጀት አመቱ 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ለማዳን አቅዶ 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ ከእቅድ በላይ ማሳካቱን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኮሚሽኑ በቀጣዩ በጀት አመት አጠቃላይ 155 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ያስቀመጠውን እቅድ ለማሳካት በተሰራው ስራ የታዩ ጠንካራ ስራዎችን ማስቀጠልና መታረም ያለባቸውን ክፍተቶች ማስተካከል ከተቻለ የበለጠ ዉጤት ለማምጣት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.