Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከአለም የምግብ ፕሮግራም ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የአለም ዓቀፍ የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ልዩ መልዕክተኛ ራሚሮ ሎፔዝ ዳ ሲልቫን በጽ/ቤታቸው አነጋግረዋል።
 
መንግስት የተናጠል የሰብዓዊ ተኩስ ማቆም ውሳኔ ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ የአለም ዓቀፍ ምግብ ፕሮግራምን ጨምሮ አጋራት የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትና ያጋጠሙ ችግሮች ላይ ተወያይተዋል።
 
ሰብዓዊ እርዳታ በአግባቡ እንዳይደርስ ዋነኛው ምክንያት የህወሃት ተደጋጋሚ ትንኮሳና ማስተጓጎል ቢሆንም ከአፋር ክልል አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመነጋገር እንዲሳለጥ መንግስት ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ መሆኑንም ሚኒስትሯ አስረድተዋል።
 
ልዩ መልዕክተኛው የአለም ዓቀፍ የምግብ ፕሮግራም ሊያግዝባቸው የሚችሉ ተጨማሪ የትብብር መስኮች ተለይተው ድጋፉን በተሻለ ለማስቀጠል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ ገልጸዋል።
 
ሚኒስትሯ በአማራ እና አፋር ክልሎች በርካታ ወገኖች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ በመሆኑ የአለም ዓቀፍ የምግብ ፕሮግራም የድጋፍ መጠኑን ይህንንም ከግምት ባስገባ መልኩ ቢሆን ጠቀሜታ እንደሚኖረው መገለጹን ከሚንስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.