Fana: At a Speed of Life!

የኪነጥበብ ባለሙያዎች በወሎ ግንባር ለሚገኙት የጸጥታ አካላት የጥበብ ስራዎቻቸውን እያቀረቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በወሎ ግንባር ለሚገኙ ለሀገር የቁርጥ ቀን ልጆች የጥበብ ስራዎቻቸውን እያቀረቡ ነው።
ባለሙያዎቹ በስፍራው ለሚገኙ የጸጥታ አካላት የሚያቀርቧቸው የጥበብ ስራዎች ወኔ ቀስቃሽ እና ሀገራዊ ይዘት ያላቸው ናቸው።

በመድረኩ ሀገራዊ አንድነትን የሚያጎሉ ቀረርቶዎች፣ ሽለላ እና  ፉክራዎች እንዲሁም  ሙዚቃዎችና ስነ ጽሁፋዊ ስራዎች እየቀረቡ ነው።

በመድረኩ የተገኙ የኪነጥበብ ባለሙያዎች የጥበብ ስራዎችን ከማቅረብ ባለፈ ለሀገር የሚከፈለውን መስዕዋትነት ለመክፈል መዘጋጀታውን  ነው ያረጋገጡት ፡፡

ሁሉም ነገር ሊኖር የሚችለው ሀገር ስትኖር በመሆኑ በሀገር ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለመመከት ሁሉም  የበኩሉን ሃላፊነት እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡

ጠላት ቀይ መሥመር አልፏል ያሉት ባለሙያዎቹ÷  ወጣቶች መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ሃይልን እና  ሌሎች አደረጃጀቶችን በመቀላቀል ሀገራቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በአፈወርቅ እያዩና ለይኩን ዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.