የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች ኮከስ አባላት ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች ኮከስ አባላት ለመከላከያ ሰራዊት የስንቅ ድጋፍ አደረጉ።
የስንቅ ድጋፋ በሶ፣ ቆሎ፣ ኮቾሮ ሲሆን፥ ብርድ ልብስን ጨምሮ የሴቶች የንጽሕና መጠበቂያ ሞዴሶችን ያካተተ ነው።
በአጠቃላይ ድጋፋ በገንዘብ ሲተመን አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊየን ብር እንደሚገመት ተገልጿል።
ድጋፋን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሽታዬ ምናለ፥ የምክር ቤቱ የሴቶች ኮከስ ሰብሳቢ ወይዘሮ አበባዬ ገዛህኝ ለመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉጂ አስረክበዋል።
የምክር ቤቱ አባላት ከዚህ ቀደም ለመከላከያ ሰራዊት የአንድ ወር ደመወዛቸውን በአጠቃላይ ሰባት ነጥብ ሦስት ሚሊየን ብር መስጠታቸውንና የደም ልገሳ ማካሄዳቸውም ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!