በደቡብ ክልል ከማዕድን ዘርፍ የሚገኘውን ሀብት ማሻሻል በሚቻልበት አግባብ ላይ ምክክር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በደቡብ ክልል ከማዕድን ዘርፍ የሚገኘውን ሀብት ለማሻሻል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በሀዋሳ የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ የማዕድን ሀብት ልማት ለሀገር የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ክልሉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡
ወርቅ በሚወጣባቸው አካባቢዎች የመሰረተ ልማት እንዲሟላ እና ሰላምና ጸጥታ በማረጋገጥ ይሰራልም ነው ያሉት፡፡
የደቡብ ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ በ2013 በጀት አመት 400 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ ለማቅረብ አቅዶ 287 ኪሎ ግራም ወርቅ ማቅረቡን ገልፀዋል።
በ2014 በጀት አመት ደግሞ 700 ኪሎ ግራም ወርቅ ገቢ ለማድረግ ታቅዷል ብለዋል፡፡
የማዕድን እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው በማዕድን ዘርፉ ሀገራዊ ፍላጎት ላይ ማተኮርና የውጪውን ገበያ ማሳደግ ቀጣይ የመንግስት የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን አንስተዋል።

ከዚህ አንጻርም ለክልሉ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ማለታቸውን ከደቡብ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!