Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በሁመራ በኩል 12 ጊዜ የማጥቃት ሙከራ ቢያደርግም ተደምስሷል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሁመራ በኩል 12 ጊዜ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ ቢያደርግም በሕዝቡና በፀጥታ አካላት ትብብር መደምሰሱን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ገለጹ።

ኮሎኔል ደመቀ ከመገናኛ ብዙሃን ጋር በነበራቸው ቆይታ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሁመራ በኩል ለ12 ጊዜ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ ቢያደርግም በሕዝቡና በፀጥታ ሀይል ትብብር መደምሱንን ተናግረዋል።

ቡድኑ ዳግም በሁመራ በኩል ጥቃት ለማድረስ ቢሞክር መቀበሪያው ይሆናል ነው ያሉት ኮሎኔሉ።

የአካባቢው ማኅበረሰብ በቂ ዝግጅት በማድረግ አሸባሪውን ቡድን የመደምሰስ አቅም ላይ ይገኛል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.