በመዲናዋ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ 8 ነዋሪዎች ቤተሰቦች የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ጀርመን አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የጉዲና አቶምሳ ቤተክርስቲያን ማሰልጠኛ ማእከል ውስጥ በተከሰተው ከባድ የጎርፍ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ 8 ነዋሪዎች የከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ ድጋፎችን አድርጓል።
በምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሚመራ የስራ ኃላፊዎች ቡድን ኃዘንተኞቹ በሚገኙባቸው ቦታዎች በመገኘት አፅናንተዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ለተጎጂ ቤተሰቦች የሚውል ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ብር ድጋፍንም የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዝዳንት ቄስ ዮናስ ይገዙ ከምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እጅ ተረክበዋል።
ድጋፉ ለቤት ኪራይ እና ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚውል ሲሆን ÷ ከ216 ሺህ ብር በላይ ወጪ የተገዙ የተለያዩ ቁሳቁስ ድጋፍም ተደርጓል።
ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቀጣይም የከተማ አስተዳደሩ ከተጎጂዎች ጎን እንደሚቆም እና ችግሩን እንደሚካፈል አስታውቀዋል።
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማም ለተጎጂዎች የ100 ሺህ ብር ድጋፍ አበርክቷል።
ከአዲስ አበባ ወደ ሆሳእና አስከሬን መሸኘቱን ተከትሎም የከተማ አስተዳደሩ ተወካዮች ስፍራው ድረስ በመጓዝ እንደሚያፅናኑ ወይዘሮ አዳነች መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
የዲስ አበባ ከተማ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንም በመዲናዋ የጎርፍ አደጋ በተከሰተባቸው በአጉስታ፣ ወይራ፣ መካኒሳ እና ጎፋ አካባቢዎች ለሚገኙ 650 ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ1 ነጥብ 5 ሚኒሊየን ብር በላይ የአይነት እና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!