“የሀገር ብሌን” የተሰኘ ሙዚቃዊ ተውኔት በጅማ ከተማ ለዕይታ ሊበቃ ነው
የጸሐፊ ተውኔት ረ/ፕ ነብዩ ባዩ ድረሰት የሆነው “የሀገር ብሌን” የተሰኘ ሙዚቃዊ ተውኔት የፊታችን ዕሑድ በጅማ ከተማ ሲኒማ ኢትዮጵያ ለዕይታ ይቀርባል።
የነጸብራቅ ኪነጥበብ ቡድን ተዋናዮች የሚተውኑት የሀገር ብሌን ቴአትር ተዋናይ ታሪኩ ጌታቸው÷ተውኔቱን ለዕይታ ለማብቃት ሰባት የልምምድ ወራትን እንደወሰደ ገልጿል።
“የሀገር ብሌን” ‘ ከ1960ዎቹ እስከ ኢትዮጵያ ሚሊኒየም ደረስ፣ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ያለፉበትን ሕይወት እያዝናና የሚያስመለክት ቁም ነገር አዘል ሙዚቃዊ ተውኔት መሆኑ ተመላክቷል።
1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ የእይታ ጊዜን በሚወስደው ተውኔቱ ላይ ቁጥራቸው 50 የሚሆኑ የጅማ ከተማ ቴአትር ክበባት ተማሪዎች ይሳተፉበታል ።
በወርቃአፈራሁ ያለው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!