Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ዶላር እናትማለን በማለት ወንጀል ሲፈጽሙ የተገኙ 2 የውጭ ዜጎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የአሜሪካን ዶላርን አሳትመን እንሰጣችኋላን በማለት የማታለል ወንጀል ሲፈጽሙ የተገኙ ሁለት የኮትዲቯር ዜጎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ፡፡
 
ግለሰቦቹ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ፍላሚንጎ በተባለ ሥፍራ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የደህንነትና የጸጥታ የጋራ ግብረ ሃይል አስታውቋል።
 
ሁለቱ የኮትዲቯር ዜጎች ከአንድ ግለሰብ ብቻ 260 ሺህ ብር በመቀበል ሀሰተኛ የአሜሪካን ዶላር ሰርተው ለመሥጠት ስምምነት በማድረግ የማጭበርበር ሥራ ሲያከናውኑ አጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.