Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል ምከር ቤት ከ2 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሐረሪ ክልል ምከር ቤት ለ2014 የስራ ዘመን ማስፈጸሚያ የሚውል ከ2 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አጸደቀ።

ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው ስድስተኛ ዓመት አንደኛ መደበኛ ጉባዔ የበጀት እቅዱን ያቀረቡት የክልሉ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልሃኪም አብዲ ናቸው።

የበጀቱ ምንጭ ከፌደራል መንግስት ድጎማ፣ ከክልሉ የውስጥ ገቢና የውጭ ብድር መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ በጀት ውስጥ 49 በመቶ ለካፒታል ወጪ፤ ቀሪው ደግሞ ለመደበኛ ስራዎች ማስፈጸሚያ እንደሆነ ተመላክቷል።

በቀረበው የበጀት እቅዱ ላይ የምክር ቤቱ ጉባኤ ከተወያየበት በኋላ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

የጸደደቀው በጀት ካለፈው የስራ ዘመን ጋር ሲነጻጸር 19 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑ ተገልጿል።

በጀቱም ለታቀዱሉት ስራዎች በአግባቡ እና በጥንቃቄ ስራ ላይ እንዲውል ምክር ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ቀጥሎ ያለው የምክር ቤቱ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆች እና ሹመቶች ላይ በመወያየት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.