የሲዳማ ልማት ማህበር የንግድ ትርኢትና ባዛር ተጀመረ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው የሲዳማ ልማት ማህበር የንግድ ትርኢትና ባዛር በሀዋሳ ከተማ ተጀምሯል።
‘ነፃነታችን ለልማታችን’ በሚል መሪ ቃል በተጀመረው ባዛር ላይ ከ200 በላይ አምራችና ነጋዴዎች ተሳትፈዋል፡፡
ልማት ማህበሩ ከኢላ ፕሮሞሽን ጋር በመሆን ያዘጋጀው ይህ ባዛር በ2014 ዓ.ም በክልሉ በትምህርት ዘርፍ ለሚሰራው ስራ የገቢ ምንጭ የሚሆን ነው ተብሏል ።
በንግድ ትርኢትና ባዛሩ ላይ የክልሉ አመራሮችና የስራ ሀላፊዎች የተገኙ ሲሆን÷ እስከ ጳጉሜን 4 ቀን እንደሚቆይ ታውቋል፡፡
በመቅደስ አስፋው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!