Fana: At a Speed of Life!

የኮቪድ -19 ወረርሽኝ አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ በመሰራጨት ላይ ይገኛል-ዶ/ር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከአዲስ አበባ መስተዳድር ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዮሃንስ ጫላ ጋር በየካና ካዛንቺስ ጤና ጣቢያዎች ያለውን የኮቪድ-19 ክትባት አገልግሎት አሰጣጥን ጎበኙ፡፡

ሚኒስትሯ በጉብኝቱ ህብረተሰቡ የክትባት አገልግሎቱ ለማግኘት በጤና ጣቢያዎቹ በመምጣት እየወሰደ መሆኑን ለማየት ችለናል ያሉ ሲሆን ÷ከክትባት አገልግሎቱ በተጨማሪም ፈጣን የኮቪድ ምርመራ ለህብረተሰቡ እየተሰጠ መሆኑ የሚበረታታ ነው ብለዋል።

በጤና ጣብያዎቹ የመደበኛ የህጻናት ክትባትና የእናቶች ጤና አገልግሎትን ጨምሮ የሚሰጧቸውን መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶች እንዲሁም በየካ ጤና ጣቢያ የሚገኘውን የደም ባንክ አገልግሎት መመልከታቸውን በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

ዶክተር ሊያ የኮቪድ – 19 ክትባት በሁሉም ጤና ጣቢያዎች በመሰጠት ላይ በመሆኑ መስፈርቱን የሚያሟሉ ሰዎች በሙሉ በአቅራቢያ ወደሚገኝ ጤና ጣቢያ በመሄድ ክትባቱን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል።

የኮቪድ -19 ወረርሽኝ አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ በመሰራጨት ላይ እንደሚገኝ ያነሱት ሚኒስትሯ ከክትባቱ በተጨማሪ ሁሉም የመከላከያ መንገዶችን አሁንም አጥብቆ እንዲተገብር አሳስበው አገልግሎቱን በትጋት እየሰጡ ላሉ ባለሙያዎች ሰራተኞችና አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.