በበጀት ዓመቱ ከ3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2013 በጀት ዓመት ከ3.6 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።
የፌዴራል ፖሊስ በ2013 በጀት ዓመት ከ3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የወንጀል መከላከል ዘርፍ የ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ማጠቃለያ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ በተካሄደበት ወቅት አስታውቋል፡፡
የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሸነር ጄነራል መላኩ ፋንታ ፥የወንጀል መከላከል ዘርፉ በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2013 ዓ.ም በርካታ ሀገራዊ ተልዕኮዎችን ይዞ ስሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።
በተለያዩ ቦታዎች የገጠሙንን የፀጥታ ችግሮችን ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በበርካታ ግንባሮች መክተናልም ነው ያሉት ፡፡
ምክትል ኮሚሽነር ጄነራሉ አያይዘውም ዋነኛ ስራችን ወንጀልን በመከላከል የሀገር ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ እንደ መሆኑ መጠን፣ ጠንካራ ጎኖችን የበለጠ አጠናክረን እንዲንቀጥልና ደካማ ጎኖችን ለመቅረፍ እንዲህ አይነቱ ግምገማ እጅግ አስተማሪ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የኮንትሮባንድ ቁጥጥርና ክትትል ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር አንሻ ቶላ ባቀረቡት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት፥ በ2013 ዓ.ም ከ67 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ አደገኛ ዕፆችና የሺሻ ዕቃዎች መያዛቸውን ገልፀዋል፡፡
በተለይም ሀሺሽ የተሰኘው አደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎች መነሻቸውን ሻሸመኔ በማድረግ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እስከ ሁመራና አዲስ አበባ ድረስ በሰፊው እያዘዋወሩ ቢሆንም በኬላዎችና በአሳቻ መንገዶች ላይ ጥብቅ ክትትል በማድረግ በርካታ ተጠርጣሪዎችን ለህግ ማቅረቡን ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት አሸባሪው የህወሃት ጁንታ ቡድን አደገኛ ዕፁን ለጦርነት ማነቃቂያ እየተጠቀመበት እንዳለም አመላክተዋል፡፡
ይሁን እንጂ ከሌሎች የፀጥታ አካላት፣ ከህብረተሰቡና ከወጣት ኃይሎች ጋር በመተባበር አዘዋዋሪዎች ተይዘው ለህግ እንዲቀርቡ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡
በተመሳሳይ ኮንትሮባንድስቶች የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በድብቅ ከቦታ ቦታ ለማሳለፍ ቢሞክሩም በተለያዩ ኬላዎች በተደረገው የተጠናከረ ፍተሻ ከ3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን ረዳት ኮሚሽነሩ ጨምረው አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም 127 ክላሽእንኮቭ፣797 ሽጉጥ፣7 ብሬን፣23 ልዩ ልዩ ቦምቦች፣7 ኋላ ቀር የጦር መሳሪያዎች፣23 ሳጥን ፈንጂዎች፣ 97 ሺህ 532 ልዩ ልዩ ጥይቶች እና ሶስት የሞርተር ፊውዞች መያዛቸውን ገልጸዋል።
ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመከላከል በተከናወኑ ተግባራት ደግሞ 16 ሚሊየን 406 ሺህ ትክክለኛና 372 ሺህ 400 ሐሰተኛ ብር እንዲሁም 689 ሺህ 289 ትክክለኛና 300 ሐሰተኛ የአሜሪካ ዶላር በተለያዩ የሀገሪቱ ኬላዎች መያዛቸውን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!




0
People Reached
141
Engagements
Boost Post
137
1 Comment
3 Shares
Like
Comment
Share