437 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሳዑዲ አረቢያ ጂዳ 84 ህጻናትን ጨምሮ 437 ዜጎች ወደ ሃገራቸው መመለሳቸው ተገለፀ፡፡
ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!