Fana: At a Speed of Life!

ወራሪው የህወሓት ቡድን በአፋር የካሉዋን ሆስፒታል በርካታ ንብረት ዘርፏል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአፋር ክልል ተጠራርጎ የወጣው ወራሪው የጁንታ ቡድን የካሉዋን ሆስፒታል የህክምና መሳሪያዎችና መድሃኒቶችን ዘርፎ መሸሹን የሆስፒታሉ ሃለፊ አቶ ሃሚድ ሆዳ ገለጹ።
በፋንቲ ረሱ ዞን ለሚገኙ አምስት ወረዳዎች አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የከላሉዋን ሆስፒታል የህክምና መሳሪያዎች በወራሪው ሃይል በመዘረፋቸው በአሁኑ ሰዓት አገልግሎት መስጠት እንደማይችል ነው ሀላፊው የተናገሩት፡፡
ጁንታው ከዘረፋቸው የህክምና መሳርያዎች መካከል አልትራሳውንድ፣ የአነስቴዥያ ማሽን፣ የቀዶ ጥገና ክፍል መሳሪያዎች፣ ማይክሮስኮፕ እና የላባራቶሪ ሲሲ ማሽን መሳርያዎች ይገኙበታል።
ወራሪው በቅርቡ በግዥ የገቡ 50 የሚሆኑ የታካሚ አልጋዎችና ፍራሾች፣ መካኒካል ቬንትሌትር ማሽን ጭምር ዘርፎ መውሰዱን ነው የሆስፒታሉ ሃላፊ ለአፋርኛ ዘጋቢያችን የነገሩት ፡፡
በጨማሪም በስቶር ውስጥ የነበረና 500 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መድሀኒት ሙሉ በሙሉ ተዘርፋል፡፡
ሆስፒታሉ በአሁኑ ሰአት አገልግሎት መስጠት በማይችልበት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አቶ ሃሚድ ገልጸው፥ የክልሉ መንግስትና የፌደራል መንግስት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡
በአሊ ሹምባሕሪ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
69
Engagements
Boost Post
53
4 Comments
12 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.