የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመጪው ዓመት የዓለም ቱሪዝም ቀን አዘጋጅ እንዲሆን ተሰየመ
አዲስ አበባ፣መስከረም 17፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ቱሪዝም ለሁለንተናዊ ዕድገት” በሚል መሪ ቃል በሲዳማ ክልል ሲከበር የቀየው የዓለም ቱሪዝም ቀን ሲጠናቀቅ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ቀጣዩ አዘጋጅ እንዲሆን ሰይሟል።
በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ በተከበረው የዘንድሮው የቱሪዝም ቀን አከባበር ሥነ ሥርዓት ላይ ፥ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተጀመረውን ገበታ ለሀገር የመዳረሻ ልማት ተከትሎ ፤ የሲዳማ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሊዳሞ በሲዳማ ክልል በተመሳሳይ አዳዲስ የመዳረሻ ልማቶችን በማስጀመር እና በልዩ ክትትል በመምራት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የዋንጫ ሽልማት እና የቱሪዝም አምባሳደርነት ማዕረግ በሚኒስቴር መስራያቤቱ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ዕለቱ በሀዋሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ሲከበር፣ በቱሪዝም ዘርፍ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ 27 ያህል ተዋንያን እውቅና እና ማበረታቻ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው፥ በሆቴል እና አስጎበብኚ ድርጅት ኢንቨስትመንት፣ በዘርፉ ማሀበራነት ፣ ከመንግስት ተቋማት እና የልማት ድርጅቶች፣ማስታወቂያና ኮሚኒኬሽን ተቋማት እንዲሁም በግለሰብ ደረጃ የእውቅና መስጠት ስነስርዓት ተከናውኗል፡፡
የቱሪዝም ቀን፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ42ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ34ኛ ጊዜ ነው ዘንድሮ የተከበረው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!