ተሰናባቹ የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት የመጨረሻ ጉባዔውን እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ተሰናባቹ የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አባላት 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 12ኛ የመጨረሻ ጉባዔውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በወቅቱ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ አፈጉባዔ አቶ ጁል ናንጋል የስራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁ የምክር ቤት አባላት የመጨረሻ አጀንዳ የሆነውን 5ኛ የምርጫ ጊዜ 6ኛ የስራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ተወያይተው በማጽደቅ የስራ ዘመናቸው ይጠነቀቃል ብለዋል።
በ5ኛው የምርጫ ዘመን በህዝብ የተመረጡና ህዝብን ሲያገለግሉ የነበሩ የምክር ቤት አባላት በነበረው ፈታኝና አስቸጋሪ ወቅቶች የክልሉን ህዝብ በማገልገላቸው በክልሉ ምክር ቤት ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ተሰናባቹ ምክር ቤት በቆይታው በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን ገልጸው ከ2008 እስከ 2013 ዓ.ም የክልል ምክር ቤት አባል በመሆን ሲያገለግሉ ለነበሩት የጉባኤ አባላት የምስጋና እና የምስክር ወረቀት እንደሚሰጥ መናጋራቸውን ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!