በመዲናዋ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል በተመለከተ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓሉ እሴቱን ጠብቆ በሰላምና አብሮነት እንዲከበር ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ አካላት ተወያይተዋል፡፡
በዚህም የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ አባ-ገዳዎች፣ ሃደ-ሲንቄዎች እና የአገር ሽማግሌዎች በውይይቱ ተሳትፈዋል፡፡
የኢሬቻ በዓል አከባበር የአብሮነት፣ የእርቅና የሰላም እሴቶችን ይዞ የሚከበር ታላቅ በዓል መሆኑ በውይይቱ ተገልጿል፡፡
የውይይት መነሻ ፅሁፍ ቀርቦ በተሳታፊዎች ሃሳብና አስተያየት ተሰጥቶበታል፡፡
የኢሬቻ በዓል ዘንድሮ በአዲስ አበባ መስከረም 22 እንዲሁም በቢሾፍቱ መስከረም 23 ቀን 2014 ዓ.ም የሚከበር ይሆናል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!