Fana: At a Speed of Life!

የሮቢት ከተማ ነዋሪዎች ወሎ ግንባር የሚገኘውን የጸጥታ አካል በግንባር ተገኝተው አበረታቱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በአምባሠል ወረዳ የሮቢት ከተማ ነዋሪዎች ወሎ ግንባር የሚገኘውን የመከላከያ ሠራዊት ፣ የክልል ልዩ ሀይሎችና የሚሊሻ አባላት በግንባር ተገኝተው አበረታተዋል፡፡

ነዋሪዎቹ በግንባር ተገኝተው ለጸጥታ አካላቱ የምሳ ግብዣ ያደረጉ ሲሆን÷ ለሠራዊቱ ያላቸውን አጋርነት በተግባር ለማሳየት በግንባር ተገኝተው ጀግኖቹን አበረታተዋል፡፡

በዚሁ የከተማዋ ነዋሪዎች የምሳ ግብዣ መርሃ ግብር የግንባሩ ከፍተኛ አመራር በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን÷ የመከላከያ ሰራዊቱ አስተማማኝ ዝግጁነት ላይ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሠዋል፡፡

ጠላት የሰፈረበት አካባቢ መቀበሪያው እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

የምሳ ግብዣውን ካዘጋጁትና ከሠራዊቱ ጋር አብረው ማእድ ከተጋሩት የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ አሠገድ ሀሠን እንዳሉት÷ ሁለት ልጆቻቸው አሸባሪውን የህወሓት ሀይል ለመደምሰስ በግንባር የተሠለፉ መሆናቸውን ለሠራዊት አባላቱ ጠቁመዋል፡፡

በእንዲህ አይነት መልኩ ከእናንተ ጋር ማዕድ ለመጋራት መታደሌ ዳግም የበርካታ ጀግኖች ልጆች እናት እንደሆንኩ ያህል እንዲሰማኝ አድርጎኛልም ነው ያሉት፡፡

በዚሁ የምሳ ግብዣ ስነ-ስርዓት ላይ ተሳታፊ የነበረው መሠረታዊ ወታደር ስንታየሁ እስክንድር በበኩሉ÷ እኛም መላው ህዝባችን እያደረገልን ያለው ሞራላዊና ቁሳዊ ድጋፍ ህዝባችን በምሽግ ውስጥ አብሮን እንዳለ ያህል እንዲሰማን ያደረገን ነው ብሏል ፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያና መላው ህዝቦቿ ሠላማዊ ህይወታቸው ይቀጥል ዘንድ ልጅ የእናት ሀገሩንም የወላጅ እናቱንም አደራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወጥቶ ያሳያል ማለቱን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.