በወላይታ ዞን ነገ ለሚደረገው ምርጫ ዝግጅት ተጠናቋል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በወላይታ ዞን ቀሪ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቁን የዞኑ ምርጫ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የ6ኛው ሃገራዊ ምርጫ አካል የሆነውንና በተለያዩ ምክንያቶች ሳይካሄድ የቆየው ይኸው ምርጫ ነገ መስከረም 20/2014 ዓ.ም ይካሄዳል።
በወላይታ ዞንም ምርጫው ባልተካሄደባቸው ስድስት የምርጫ ክልሎች 467 የምርጫ ጣቢያዎች ነገ ከማለዳው 12 ጀምሮ ድምፅ እንደሚሰጥ የጽህፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ሻንካ ተናግረዋል።
ቀሪውን ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ለምርጫ አስፈፃሚዎች ስልጠና መስጠት፣ ከተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር ማካሄድ እና ሌሎችም ተሰርተዋል ብለዋል።
በመሆኑም ከትላንትና ጀምሮ የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶች ሥርጭት እየተካሄደ ሲሆን÷ ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አክለው ገልፀዋል።
በ6ቱም የምርጫ ክልሎች ድምፅ ለመስጠት የተመዘገበ ማንኛውም መራጭ በተመዘገበበት የምርጫ ጣቢያ በመገኘት በምርጫው በመሳተፍ ዲሞክራሲያዊ መብቱን እንዲጠቀም ጠይቀዋል።
በማስተዋል አሰፋ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!