ድምጽ ለመስጠት የምርጫውን ቀን በጉጉት እየጠበቅን ነው- የምዕራብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች
አዲስ አበባ፣መስከረም 19፣2014 (ኤፍ ቢሲ)የሚፈለጉትን የፖለቲካ ፓርቲ በነጻነት ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን በምእራብ ኦሞ ዞን የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተናገሩ፡፡
ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም የህዝብን ድምጽ በጸጋ በመቀበል ለአካባቢ ሰላም እና ልማት የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
ባለፈው ሰኔ ወር ምርጫ ባልተካሄደባቸው እና ነገ ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች አንዱ የሆነው የምእራብ ኦሞ ዞን÷ በ5 የምርጫ ክልሎች በ127 የምርጫ ጣቢያዎች 127 ሺህ 816 መራጭ ድምጽ ለመስጠት ተመዝግቧል።
መራጮችም ምርጫው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚያበረክቱ ተናግረዋል።
ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም የህዝብን ድምጽ በማክበር ለአካባቢ ልማት እና ሰላም የበኩላቸውን ድርሻ ሊያበረክቱ ይገባል ተብሏል።
ህዝብ ለበርካታ አመታት ሲጠይቅ የቆየው በቅርበት የመዳኘት እና የመልማት ፍላጎት እውን ለመሆን የደቡብ ምእራብ ዞኖች የክልልነት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ በዚህ ምርጫ መካተቱም እንዳስደሰታቸው መናገራቸዉን የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!