የመተከል ዞንና የፓዊ ወረዳ የብልፅግና ፖርቲ ሴቶች ሊግ ለመከላከያ ሰራዊት የስንቅ ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ መሰከረም 23፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የመተከል ዞን እና የፓዊ ወረዳ የብልፅግና ፖርቲ ሴቶች ሊግ ለመከላከያ ሰራዊት የተለያዩ የደረቅ ስንቅ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የተዘጋጀውን ደረቅ ስንቅ የተረከቡት በስፍራው የሚገኝ የሰራዊት ክፍል ምክትል አዛዥ ለአፕሬሽናል ኮሎኔል መልካሙ በየነ ÷የመተከል ዞን ሴቶች ለሰራዊቱ እያደረጉ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
የመተከል ዞን ብልፅግና ፖርቲ ሴቶች ሊግ አስተባባሪ ወይዘሮ ነገሪ ፉፋ÷ለመተከል ዞን ሕዝብ ሰላም ለሚተጋው የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!