Fana: At a Speed of Life!

ታንዛኒያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት አላት – አምባሳደር ሊበርታ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በታንዛኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ ከታንዛኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሊበርታ ሙላሙላ ጋር ውይይት አድርገዋል።

አምባሳደር ዮናስ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታን በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የሁለቱ ሀገራትን ግንኙነት ለማጠናከር በተለያየ ጊዜ የተፈራረሙትን ስምምነቶች ወደ ትግበራ ምዕራፍ ማሸጋገር እንደሚያስፈልግ፣ ሁለቱ ሀገራት እምቅ የቱሪዝም አቅማቸውን ተጠቅመው የጋራ ተጠቃሚ ለመሆን እንዲሁም በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍም በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።

ሚኒስትር አምባሳደር ሊበርታ በበኩላቸው÷ ታንዛኒያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት ያላት መሆኑን ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን መድረኮች በትብብር የመስራት ልምዳቸውን ይበልጥ በማጠናከር ለጋራ ተጠቃሚነት እንደሚሰሩ አምባሳደሯ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.