የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ሲመትን የታደሙ የሃገራት መሪዎች ወደሃገራቸው መመለስ ጀመሩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሲመትን የተለያዩ ሃገራት መሪዎች ትናንት በመስቀል አደባባይ ተገኝተው ታድመዋል፡፡
የጂቡቲ ፕሬዚደንት እስማኤል ኦማር ጊሌህ በተካሄደው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዓለ ሲመት ላይ ታድመው ዛሬ ወደ ሃገራቸው አቅንተዋል።
በወቅቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለፕሬዚደንቱ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።
በአሸኛኘት ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ተገኝተዋል።
በተያያዘም የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃን ሚኬል ሳማ ሉኮንዴ ትናንት ምሽት ወደ ሃገራቸው ሲያቀኑ አሸኛኘት እንደተደረገላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!