ሁለት የትምህርት ተቋማት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች 5 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ እና የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኤጀንሲ አሸባሪው ህወሓት በፈፀመው ወረራ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች 5 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አደረጉ።
የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶክተር ተሻለ በሬቻ እንዳሉት÷ አሸባሪው ህወሓት በፈፀመው ወረራ ከሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች ምግብና ምግብ ነክ፣ የንፅህና መጠበቂያ እና አልባሳት ድጋፍ ተደርጓል።
የተደረገው ድጋፉም ሁለት ነጥብ 5 ሚሊየን እንደሚገመት መናገራቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
አሸባሪውን ህወሓት ለመቅበርና ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ከኢትዮጵያ ውስጥ እና በውጭ ያሉ ዜጎች ሊተባበሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ አሸባሪው ህወሓት ላፈናቀላቸው ዜጎች 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሚገመት ምግብ፣ አልባሳትና የንፅህና መጠበቂያዎችን ድጋፉ ማድረጉን ገልፀው÷ በቀጣይም ድጋፉ እንደሚጠናከር አረጋግጠዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!