የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ1ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሠመራ ዩኒቨርሲቲ በአሸባሪው ትህነግ ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አደረገ፡፡
ዩኒቨርሲቲው አሸባሪው ትህነግ ባደረሰው ውድመት ከሰሜን ወሎ ዞን አካባቢ ተፈናቅለው በደሴ ከተማ ለሚገኙ ዜጎች ድጋፍ አድርጓል፡፡
የዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቡቦከር ያሲን “ድጋፋችን ከደረሰው አደጋ አንጻር በቂ ነው ባይባልም የወገን አለኝታነታችንን ማሣያ ነው” ብለዋል፡፡
ዳይሬክተሩ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብና የአልባሳት ድጋፍ መደረጉንም አስረድተዋል፡፡
በቀጣይም ዩኒቨርሲቲዎች የእርስ በእርስ ትብብር እንዲኖራቸው እንደሚሠራም ነው ያላቸውን እምነት የገለጹት፡፡
የተደረገውን ድጋፍም ለተፈናቃዮች ለማድረስ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ማስረከቡን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!