Fana: At a Speed of Life!

ሚዲያችን ሀገርን ከችግር ለመታደግ እና ለማልማት ሊተጋ ይገባል – የኦቢኤን ዋና ዳይሬክተር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የሀገራችን ሚዲያ ኢትዮጵያን ከችግር ለመታደግና ልማቷን ለማፋጠን በትጋት መስራት እንደሚጠበቅበት የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤን) ዋና ዳይሬክተር  አቶ ዝናቡ አስራት ተናገሩ።

ለዜጎቿ ምቹ የሆነች ሀገር ለመገንባት ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚያደርጉ ሚዲያዎች ሀገራችን ያሰፈልጋታል ያሉት አቶ ዝናቡ፥ ድርጅታቸው ከሰሜን ወሎ ዞን ተፈናቅለው በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ወገኖች ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የተለያየ የምግብ ድጋፍ ዛሬ አስረክበዋል።

የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ መላ ሰራተኞችና አመራሮች በመተባበር 125 ኩንታል ስንዴ ፣ 18 ኩንታል ዱቄት፣ 307 ኩንታል በቆሎ፣ 50 ኩንታል ማሽላ በጥቅሉ 500 ኩንታል የምግብ ድጋፍ አድርገዋል።

አቶ ዝናቡ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፥ ለወገን ደራሽ ወገን ነውና ይህ የመጀመሪያችን ነው፤ በቀጣይም አብረናችሁ ነን ሲሉ ተፈናቃይ ወገኖችን አበረታተዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ወልደ ተንሳኤ መኮነን ስለተደረገው ድጋፍ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ አመራሮችንና ሰራተኞችን አመስግነዋል።

በአለባቸው አባተ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.