Fana: At a Speed of Life!

የሰንደቅ ዓላማ ቀን ስናከብር ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይላት አንገታቸውን የሚደፉበት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ነው – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የሰንደቅ ዓላማ ቀን ስናከብር ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይላት አንገታቸውን የሚደፉበት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ እንደሆነ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞች “በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉዓላዊነት ለሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል 14ኛው የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን ሲያከብሩ ነው።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ ሰንደቅ ዓላማ ክብር በየተሰማራበት የሥራ መስክ ታላቅ ስኬት ማስመዝገብ ይጠበቅበታል ነው ያሉት።

14ኛው የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶች ፣ በወታደራዊ ካምፖች ፣ ኤምባሲዎች እና በሌሎች ተቋማት እየተከበረ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.