Fana: At a Speed of Life!

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ማሳሰቢያ ሰጠ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሙዩኒኬሽን እና የመገናኛ መሳሪያዎች በእጃቸው የሚገኝ ግለሰቦች እና ተቋማተ በ15 ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግቡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አሳሰበ።

በኢትዮጵያ ህልዉና አደጋን ለመከላከል፣ ስጋት እና ሉአላዊነት ጥሰት ለመከላከል ሁሉን አቀፍ የጥንቃቄ እርምጃዎች መዉስድ አስፈላጊ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ገልጿል፡፡

በዚህም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የኢንፎርሜሽን እና የኮሙዩኒኬሽን መሳሪያዎችን ሲመዘግብ እና ሲቆጣጠር የቆየ ቢሆንም አሁናዊ ይዞታን ለማወቅ እና እነዚህ የኮሚዩኒኬሽን መሳሪያዎች በአሸባሪዎች እና ገብረ-አበሮቻቸዉ ለሽብር አላማ እንዳይዉሉ መሳሪያዎቹን እንደገና መመዝገብ እና በሚመለከተዉ አካል እጅ ስለመኖሩ ማወቅ ኤጀንሲዉ ተገቢ ሆኖ አግኝቶታል።

በመሆኑም የኮሙዩኒኬሽን እና የመገኛኛ መሳሪያዎች በእጁ የሚገኝ ማንኛዉም ግለሰብ፣ ተቋም፣ ኤምባሲ ወይም ዲፕሎማት፣ በመንግስታዊም ሆነ በግል ተቋማት ጥበቃ ላይ የተሰማሩ አካላት፣ በዘርፉ የተሰማሩ አስመጪዎች እና ላኪዎች በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እንዲያሳዉቁ አሳስቧል፡፡

በዚህም ወታደራዊ የቅኝት መሳሪያዎች ፣ወታደራዊ እና ሲቪል የመገናኛ መሳሪያዎች፣ቪሳት እና ቢጋንና ድሮኖች በግለሰቦች እጅ ወይም በተቋማት ውስጥ ሲጠቀም ያየ ማንኛዉም አካል ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በነጻ ስልክ ቁጥር 933 ወይም 0113851193 ፣ 0904049625 እና 0114701321 ማሳወቅ ይጠበቅበታል ነው የተባለው።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.