Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሃት በንድፈ ሃሳብ ያፈረሳትን አገር በተግባር ለመድገም የሚያደርገው ጥረት አይሳካም

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “አሸባሪው ህወሃት በንድፈ ሃሳብ ያፈረሳትን አገር በተግባር ለመድገም የሚያደርገው ጥረት ፈፅሞ አይሳካም” ሲሉ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሱ ጥላሁን ተናገሩ።

አሸባሪው ህወሃት በአሁኑ ወቅት ወረራ የፈጸመው አማራና አፋር ክልሎች ቢሆንም የመጨረሻ ግቡ ግን ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው።

በጀግኖች ደምና አጥንት ተገንብታ የቆየችውን ታሪካዊ አገር የማፈራረስ ህልሙን ለማሳካት ከጥፋት አጋሮቹ ጋር ሆኖ እየሞከረ መሆኑንም ተናግረዋል።

“ሆኖም ኢትዮጵያዊያን የሚዝል ክንድ፤ የሚበታተን ህብረት ስለሌለን በጋራ ክንዳችን አሸባሪውን ድል እናደርገዋለን” ብለዋል።

የአሸባሪው ህወሃት የተደበቀ ማንነት ሴራ፣ እርስ በርስ ማጋጨት፣ አሉባልታ እና ክህደት መሆኑን የጠቀሱት አቶ ንጉሱ በቅርቡ በማይካድራና ጋሊኮማ እንዲሁም ሌሎች አካባቢዎች በንጹሀን ላይ የፈፀመውን ጭፍጨፋ ለማሳያነት ጠቅሰዋል።

በኢኮኖሚና በስነ ልቡና ሊያንኮታኩተው የመጣውን ወራሪ ሃይል በመደምሰስ ህዝቡ የተለመደ የአርበኝነት ታሪኩን እያሳየ መሆኑንም መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አሸባሪው ህወሃት ትልቁ የጦርነት ስልቱ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በመሆኑ ይህንን ስልት በመጠቀም ዛሬም ሽብር እየፈጠረ መሆኑን ጠቁመው፤ “ህዝቡ አሉባልታና የሽብር ቡድኑ መገለጫ መሆኑን ማጤንና መመርመር አለበት” ሲሉ አስገንዝበዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.