Fana: At a Speed of Life!

ዘመናዊ መኖሪያ ቤታቸውን ለ42 ተፈናቃዮች መጠለያነት ያዋሉት ግለሰብ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደብረ ብርሃን ነዋሪው አቶ ኤፍሬም ጌታቸው ለራሳቸው መኖሪያ ያስገነቡትን ዘመናዊ መኖሪያ ቤታቸውን ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ተፈናቃዮች “ቤት ለእምቦሳ” ብለው እንዲያርፉበት አድርገዋል።
የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ እያደረሱት ያለው ኢ-ሠብዓዊ ድርጊት በሰው ልጅ አዕምሮ የማይታሰብ ዘግናኝ ነው፤ በተቃራኒው የአቶ ኤፍሬም ሠብዓዊነት እጅን በአፍ ያስጭናል።
በንግድ ስራ የተሰማሩ አቶ ኤፍሬም ጌታቸው ሊኖሩበት ያስገነቡትን ቅንጡ መኖሪያ ቤት ሊገቡበት ሽር ጉድ ላይ ነበሩ።
ይሁንና ለዓመታት ጥረው ግረው ባፈሩት አንጡራ ሀብታቸው ያስገነቡትን ዘመናዊ ቤት አሸባሪው የህወሓት ቡድን ከመኖሪያቸው ያፈናቀላቸው ንጹሃን ወገኖቻቸው “ቤት ለእምቦሳ” ብለው እንዲገቡበት ፈቅደዋል።
የህፃናት ለቅሶ፣ የእናቶች ሲቃ፣ የአባቶች መብሰልሰል ልባቸውን የነካው እኒህ ሰው ወገን እያለቀሰ ደስታ የለም በማለት ወደ አዲሱ ቤታቸው እንደወሰዷቸው ይናገራሉ።
አቶ ኤፍሬም የሙያ አጋሮቻቸውና የቅርብ ጓደኞቻቸውን በማስተባበር በሌላ የጓደኛቸው ቤትም 52 ተፈናቃዮች እንዲጠለሉ አድርገዋል።
“አገር ከሌለች ሀብት፣ ንብረት፣ ቤተሰብ መመስረት የሚባል ነገር የለም” የሚሉት አቶ ኤፍሬም ሁሉም ለወገኑ የቻለውን እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
በአቶ ኤፍሬም መኖሪያ ቤት የተጠለሉት ተፈናቃዮች ለተደረገላቸው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።
ከቆቦ ጀምሮ በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች መንገላታታቸውን፤ ለከፋ ችግር ተዳርገው መቆየታቸውን ገልጸዋል።
አቶ ኤፍሬምን ‘እኛም አናውቀውም እሱም አያውቀንም’ የሚሉት ተፈናቃዮች በችግራችን ወቅት የክፉ ቀን ደራሽ በመሆን የወገን አለኝታነቱን አሳይቶናል ብለዋል።
የአቶ ኤፍሬምን መልካምነት ለመግለጽ ቃላት ያጥረናል፣ ሰው በመሆናችን ብቻ እኩል ማስተናገድ ፈጣሪ የሚወደው ነው ሲሉም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ብዙ ኤፍሬሞች ያስፈልጓታል ያሉት ተፈናቃዮች ቤታቸውን ሰጥተው፣ ከራሳቸው ቀለብ ሰፍረው፣ የታመሙትን የሚንከባከቡና ሀኪም ቤት ወስደው የሚያሳክሙ ቅን ሰው መሆናቸውን መስክረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.