የክፍለ ከተማዉ ነዋሪዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ልማት ማህበር (አልማ )አስተባባሪነት የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወርቁ ሰፈር ነዋሪዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች 4ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብና የአልባሳት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል ፡፡
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የአልማ የድጋፍ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሙሉጌታ ወልደሃና፥ የወርቁ ሰፈር ነዋሪዎች አዋተው የዕለት ምግብና አልባሳት ደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች የተበረከተ ድጋፍ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
በአረመኔው የህወሃት ቡድን እኩይ ሴራ ምክንያት ተፈናቅለው ለሚገኙ ወገኖች የሚደረገው ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት የድጋፉ አስተባባሪ፥ ሌሎች አካባቢዎችም በሚችሉት አቅም ለተፈናቀሉ ወገኖች እንዲደርሱ መልእክት አስተላልፈዋል ፡፡
በታለ ማሞ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!