የህዳሴው ግድብ ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር ለማደግ ያስቀመጠችውን መርህ የሚያግዝ ነው
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ከቀጠናው አገራት ጋር ተሰናስላ ለማደግ ያስቀመጠችውን መርህ የሚያሳልጥ ፕሮጀክት መሆኑን የአፍሪካ እና እስያ ጥናትና ምርምር ማዕከል ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተፈራ ተናገሩ።
ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተፈራ የህዳሴ ግድብ የግጭት ምክንያት ሳይሆን በጋራ የመልማትና የጋራ ተጠቃሚነትን እቅድ ያነገበ ፕሮጀክት መሆኑን ገልፀዋል።
ግድቡ የቀጠናውን አገራት በብዙ መልኩ ተጠቃሚ የሚያደርግ ግዙፍ የአፍሪካ ፕሮጀክት ሲሆን ከብክለት የፀዳ፣ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን እውን የሚያደርግ መሆኑን ይገልፃሉ።
የግድቡ ዓላማና ጠቀሜታው ይህ ሆኖ እያለ ኢትዮጵያ ከአባይ ምንም አይነት ተጠቃሚነት እንዳይኖራት እየሰሩ ያሉ አገራት መኖራቸውን ጠቁመዋል።
ይህም የኢትዮጵያን ምጣኔ ሃብታዊ ጥንካሬና ከእድገቷ ጋር ሊመጣ የሚችልን የኃይል ሚዛን ሊቀይር ይችላል ከሚል ስጋት የሚመነጭ መሆኑን ማብራራታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ሥራ ሲጀምር ኢትዮጵያ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎችን እንድታንቀሳቅስ ያስችላታል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ ጂኦ-ፖለቲካዊ አቀማመጧ እና ያላት ሰፊ የህዝብ ቁጥር ለአረቡ ዓለም፣ ለእስያ፣ ለአውሮፓ፣ ለመካከለኛው ምስራቅና ደቡባዊ የአፍሪካ ክፍል መግቢያ በር በመሆኗ ተመራጭ መዳረሻ ያደርጋታል ብለዋል።
የቀጠናውን አገራት አዎንታዊ ግንኙነት በማጠናከርም የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ግንኙነት ወደ አንድ ደረጃ ከፍ ማድረግ እንደሚያስችል አመላክተዋል።
ኢትዮጵያውያን ለግድቡ መጠናቀቅ እያደረጉት ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክረው በማስቀጠል ከግብ እንዲደርስ ማድረግ እንዳለባቸውም ጥሪ አቅርበዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!