የጂቡቲ ዜጎች በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የምግብና አልባሳት ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጂቡቲ ዜጎች አሸባሪው ህወሓት በከፈተው ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን የፀጥታ ኃይሎች ከ394 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረጉ።
የጅቡቲ ዜጎች ድጋፉን ያደረጉት አሸባሪው ህወሓት አገር የማፍረስ እኩይ ተልዕኮውን ለማሳካት በከፈተው ጦርነት ጉዳት ደርሶባቸው በዱብቲ ሆስፒታል በሕክምና ላይ ላሉ ኢትዮጵያውያን የፀጥታ ኃይሎች ነው።
ድጋፉ 50 ፍየሎችን፣ 20 ኩንታል ሩዝ፣ 10 ካርቶን ፓስታ፣ አልባሳትና ጫማዎችን ያካተተ መሆኑ በርክክቡ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።
ድጋፉን ያስተባበሩት ሐጂ አሎ ያዮ ለዱብቲ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር መሐመድ ዩሱፍ አስረክበዋል።
አሸባሪው ህወሓት በአፋርና አማራ ክልሎች የከፈተው ጦርነት ከኢትዮጵያ አልፎ የቀጠናውን አገራት ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ እንደሚጥል መግለጻቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።
የሽብር ቡድኑ የፈጸመውን ወረራ ለመመከት ሲታገሉ ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ያለንን አጋርነት በተግባር ለማሳየት ድጋፉን ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!