Fana: At a Speed of Life!

ከወለድ ነጻ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ከ117 ቢሊየን ብር በላይ ቆጥበዋል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፋይናንስ አካታችነትን ተደራሽ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ዕድገት እንዲፋጠን በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ዕውቀት፣ ክህሎትና ሀብታቸውን አስተባብረው እንዲሰሩ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ጥሪ አቀረቡ። ጥሪው የቀረበው ‘አካታች የፋይናንስ…

አንዲት እናት 3 ልጆችን በሠላም ተገላገለች

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማበር ወረዳ ዶቃቂት ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወይዘሮ ትዝታ ንጉሴ 2 ሴቶች እና 1 ወንድ ልጅ በሠላም ተገላግላለች፡፡ ወይዘሮ ትዝታ የሕክምና ክትትል ስታደርግ በቆየችበት ደብረ-ሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል መውለዷም ነው…

በኢትዮ-ጂቡቲ የድንበር አገልግሎት ግንባታ ለማስጀመር የሚያስችል ድጋፍ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮ-ጅቡቲ ጋላፊ ድንበር የአንድ - አለቅ የድንበር አገልግሎት ግንባታ በ3 ነጥብ 2 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ በጀት እንዲጀመር “ከኮሜሳ” ጋር ስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡ በቀጣይ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም እየታየ ድጋፉ እንደሚቀጥልም የንግድና ቀጣናዊ…

“የህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያውያን መብራትም እራትም ነው”- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “የህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያውያን መብራትም እራትም ነው" ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ። የታላቁ የህዳሴ ግድብ 2ኛ ተርባይን በዛሬው እለት ሃይል ማመንጨት ጀምሯል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎትም የእንኳን ደስ አላችሁ…

ቻይና ከአንድ የአሜሪካ ሥጋ አቅራቢ ኩባንያ ምርት እንዳይገባ አገደች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ቻይና ከአንድ የአሜሪካ ኩባንያ የቁም እንስሳት የሥጋ ውጤት ወደ ሀገሯ እንዳይገባ አግዳለች፡፡ የቻይና የጉምሩክ ባለሥልጣናት ከኩባንያው የሚገቡ የሥጋ ውጤቶችን ያገዱት “ራክቶፓሚን” የተሠኘ የተከለከለ ንጥረ ነገር በማግኘታቸው መሆኑን ዛሬ…

ፊንላንድ እና ስዊድን ኔቶን እንዲቀላቀሉ ከአሜሪካ ይሁንታ አገኙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ፊንላንድ እና ስዊድን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) እንዲቀላቀሉ በሚያስችሉት ፕሮቶኮሎች ላይ መፈረማቸው ተገለጸ፡፡ ሀገራቱ የቃል ኪዳን ድርጅቱን እንዲቀላቀሉ ከዴሞክራቲክ እና ከሪፐብሊካን…

በኦሮሚያና በደቡብ ለድርቅ ተጋላጭ አካባቢዎች የእንስሳት መኖ እየለማ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች ለድርቅ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የእንስሳት መኖ ልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የግብርና ቢሮ ኃላፊዎች ገለጹ። የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ አበራ ወርቁ ÷ የእንስሳትን ምርታማነት ለማሳደግ ፣ ዝርያ ለማሻሻልና…

በኦሮሚያ ክልል እስካሁን 5 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዚህ ዓመት የክረምት ወራት የእርሻ ልማት መርሐ ግብር እስካሁን 5 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር መሸፈን መቻሉ ተገልጿል፡፡ በዚህ ዓመት የክረምት ወቅት በአጠቃላይ በክልሉ የሚገኘውን 6 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር ያህል የእርሻ መሬት በዘር…

እህል የጫኑ ተጨማሪ ሁለት መርከቦች ከዩክሬን ተነስተዋል

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት ተጨማሪ ሁለት የወጪንግድ እህል የጫኑ መርከቦች ከዩክሬን ጥቁር ባሕር ወደቦች መነሳታቸውን የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ እንደገለጸው በተደረሰው ሥምምነት መሠረት የመጀመሪያዋ የወጪ ንግድ እህል የጫነች መርከብ…

በ“ቴክስት ሪኮግኒሽን” ቴክኖሎጂ ላይ በትብብር ለመሥራት ከቻይናው ዩኒቨርሲቲ ጋር ሥምምነት ተደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከቻይናው ሁዌዦንግ ዩኒቨርሲቲ ጋር በ“ቴክስት ሪኮግኒሽን”ቴክኖሎጂ ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡ ስምምነቱ በቴክስት ሪኮግኒሽን ቴክኖሎጂ ላይ በቻይና እና…