Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የመጀመሪያ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ሥራውን በይፋ መጀመር የሚያስችለውን ጉባኤ ማካሄድ ጀምሯል፡፡ በጉባዔው ላይ የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ፣ የብሄራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ፍሬሕይወት…

የዴንማርክ መንግስት በኢትዮጵያ ንጹሕ የመጠጥ ውሃ ለማዳረስ 10 ሚሊየን ዶላር ለገሰ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዴንማርክ መንግስት በኢትዮጵያ ንጹሕ የመጠጥ ውሃ በዘላቂነት ለማዳረስ የሚውል 10 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መለገሱን ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡ ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ፥ የዴንማርክ መንግስት ላደረገው ድጋፍ ትልቅ ምሥጋና አቅርቦ ፣ ንጹሕ የመጠጥ ውሃ…

በአዲስ አበባ ዘመናዊ የኢንዱስትሪ መንደር በ93 ሄክታር መሬት ላይ ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽኅፈት ቤት በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ክፍለ ከተማ ዘመናዊ (ስማርት) የኢንዱስትሪ መንደር በ93 ሄክታር መሬት ላይ ለመገንባት ማቀዱን አስታወቀ፡፡ በዘንድሮው ዓመት በ42 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት ላይ…

ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኢንቨስትመንት አማራጮችን የማስተዋወቅና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኢንቨስትመንት አማራጮችን የማስተዋወቂያና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር አካሄደ። በመርሐ-ግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እንዲሁም…

ሕንድና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚችሉበት አግባብ ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕንድና ኢትዮጵያ በልማት እንዲሁም በበርካታ ዘርፎች የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚችሉበት አግባብ ላይ ተወያዩ። ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ጃይሻንካርን በጽኅፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡…

ኢትዮጵያ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የምግብና መጠጥ አውደ ርዕይ ላይ ምርቶቿን አስተዋወቀች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የምግብና መጠጥ አውደ ርዕይ ላይ ምርቶቿን ማስተዋወቋን በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ። ለሦስት ቀናት በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ጋልገር ስብሰባ ማዕከል በተካሄደው አውደ ርዕይ ላይ ኢትዮጵያ ቡና፣…

ሽብርተኛና ለሀገር ደኅንነት አደጋ በሆኑ ተላላኪ ኃይሎች ላይ የሚወሰደው ሕግ የማስከበር እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በየትኛውም አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ሽብርተኛ እና የአገር ደኅንነት አደጋ የሆኑ ተላላኪ ኃይሎች ላይ የሚወሰደው ሕግ የማስከበር እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ገለጹ። የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ…

በኢትዮጵያ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ የተጎዱ ሰዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም መሥራት ይገባል- የአውሮፓ ኅብረት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ የተጎዱ ሰዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም መስራት እንደሚገባ የአውሮፓ ኅብረት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር ጃኔዝ ሌናርቺቺ ገለጹ። ኮሚሽነሩ በሶማሌና ትግራይ ክልሎች በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ሳቢያ ጉዳት…

ከፈረንጆቹ 1979 ወዲህ በስፔን የኮሌራ በሽታ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከሰተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፈረንጆቹ 1979 ወዲህ በስፔን ካስቲል-ላ ማንቻ ግዛት የኮሌራ በሽታ ለመጀመሪያ ጊዜ መከሰቱ ተገለጸ፡፡ አንድ ሕፃን የቧንቧ ውሃ በመጠጣቱ ምክንያት መታመሙን እና በምርመራም የኮሌራ በሽታ መሆኑ መለየቱን የግዛቲቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡…

የሀገራት በጠላትነት መፈራረጅ ለዩክሬን መፍትሄ አያመጣም – ቻይና

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገራት መካከል ያለው ጠላትነት በዩክሬን ለተከሰተው ቀውስ ዕልባት እንደማስገኝ ቻይና አስጠነቀቀች። የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት በዩክሬን ጉዳይ ላይ መግለጫ አውጥቷል፡፡ በመግለጫው ወቅት በተመድ የቻይና ምክትል ቋሚ ተጠሪ የሆኑት ዳይ ቢንግ ÷…